Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-8

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,044 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ ዘጠኝ (19) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ ስድስት (306) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች አስራ አምስት (15) ወንድ እና አራት (4) ሴት ናቸው፡፡ በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ  ከ16 እስከ 55 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 2 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል (ጊንጪ ከተማ፣ ደንዲ ወረዳ፣ ምዕራብ ሸዋ ዞን)፣ 3 ሰዎች ከትግራይ ክልል (ማይ ካድራና ሰቲት ሁመራ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል (መተማ ለይቶ ማቆያ) እና 11 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው15
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው2
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው2
 ድምር19

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አንድ (1) ሰው ከኦሮሚያ ክልል ከበሽታው ያገገመ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አስራ ሶስት (113) ነው።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ53,029
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ4,044
በዛሬው  ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ19
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ186
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ1
በአጠቃላይ ያገገሙ113
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ5
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር306

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ  ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።   

  • መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
  • መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 8 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *