Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-7

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,707 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ አምስት (15) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ ሰማንያ ሰባት (287) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ እድሜያቸው ከ17 እስከ 38 ዓመት የሆኑ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 8 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 2 ሰዎች ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል (ጉባ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከአፋር ክልል (ሰመራ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል (ሜታ ለይቶ ማቆያ) እና 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ይገኛሉ።

የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታየታማሚዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው7
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው7
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው1
 ድምር15

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አራት (4) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አስራ ሁለት (112) ነው።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ48,985
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ3,707
በዛሬው  ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ15
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ168
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ4
በአጠቃላይ ያገገሙ112
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ5
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር287

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ  ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።   

  • መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
  • መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 7፣ 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *