ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2650 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት (2) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ ስልሳ ሶስት (263) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሁለቱም ወንድ ኢትዮጵያዊያን እድሜያቸው 24 እና 33 ዓመት የሆኑ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው አንደኛው የትግራይ ክልል ነዋሪና የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ ሲሆን ሁለተኛው ከሶማሌ ክልል (ጂግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ነው።
የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የተጋላጭነት ሁኔታ | የታማሚዎች ቁጥር |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው | 2 |
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው | 0 |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው | 0 |
ድምር | 2 |
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሁለት (2) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ስምንት (108) ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 41,698 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 2650 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 2 |
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ | 148 |
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ | 0 |
አዲስ ያገገሙ | 2 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 108 |
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 5 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 263 |
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።
- መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
- መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
- መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
- መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ግንቦት 5፣ 2012 ዓ.ም