Categories
Amharic

የአውሮፓ ኅብረት ለኢጋድ አባል ሀገራት የሕክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

የልማት መንግስታት ባለስልጣን (IGAD) በኢትዮጵያ የሚደረገውን የኮቪድ-19 ምላሽ የሚያግዙ ከ13 ሚሊዮን ዩሮ በላይ የሚያወጡ የሕክምና መገልገያ መሳሪዎችን ድጋፍ አደረገ፡፡ ድጋፉ የአውሮፓ ህብረት እና የልማት መንግስታት ባለስልጣን የኮቪድ 19 የጤና እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ላይ የሚሰጡት ምላሽ አካል ነው፡፡

የ IGAD ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ መሳሪዎቹን ለጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ አስረክበዋል፡፡

የግል የሕክምና ደህንነት መጠበቂያዎች፣ የፊት ማስኮች፣ አምቡላንሶች፣ ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪ፣ ወ.ዘተ ከተለገሱት ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኩል የሚሰራጩ ይሆናል፡፡ የመጀመሪያው ዙር ስርጭት ወደ ሀገር መግቢያ በሮች አከባቢ እና ድንበር ላይ ለሚገኙ የስደተኞች ካምፕ የሚሰራጩ ሲሆን እንደ አጠቃቀማቸው ደግሞ በድጋሚ የሚሰራጭ ይሆናል፡፡

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#አሁንምእንጠንቀቅ

#COVID19Ethiopia

#Directive30

#COVID19VACCINE

#NOMASKNOSERIVCE  

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *