የተዛባ መረጃ እና ማስተካከያ

መረጃ 1 - የፊት ማስክ ሙሉ በሙሉ ከበሽታው ይከላከላል

እውነታ - የፊት ማስኮች ጭምብሎች ከሌሎች የመከላከያ መንገዶች ጋር በማጣመር ልንጠቀምባቸው ይገባል፡፡

መረጃ 2 - አንድ ሰው እንደ እንቁላል፣ ዶሮ፣ አሳና ሥጋ ያሉ ምግቦችን በመብላት በበሽታው ሊጠቃ ይችላል

እውነታ - በአሁኑ ጊዜ የኮቪድ-19 በሽታ በእንቁላል፣ በዶሮ እና በስጋ በመብላት ይተላለፋል የሚል ምንም ማስረጃ የለም፡፡ሆኖም ምግቦችን በሚይዙበት ወይም በሚዘጋጁበት ጊዜ እንደማንኛውም ጊዜ፣ጥሩ የንጽህና አጠባበቅ ልምዶችን መከታተል አስፈላጊ ነው (ለምሳሌ እጅዎን እና እቃዎችን ዘወትር ማጠብ፣ ጥሬ ሥጋን ከሌሎች ምግቦች መለየት፣ ወደ ትክክለኛው የሙቀት መጠን ማብሰል) አስፈላጊ ነው፡።

መረጃ 3 - የኮቪደ-19 በሽታ ከቤት እንስሳት ወደ ሰው ይተላለፋል

እውነታ - እንደ ውሾች ወይም ድመቶች ያሉ የቤት እንስሳት በሰዎች ላይ በሽታ እያስተላለፉ እንደሆነ የሚያሳይ መረጃ ባይኖርም አንዳንድ ጥናቶች ቫይረሱ እንስሳትንም እንደሚይዙ ይጠቁማሉ፡፡ስለሆነም፣ ከእንስሳት ጋር ያልዎትን ንክኪ መቀነስ እና የእጅዎትን ንጽህና መጠበቅ ይኖርብዎታል።

መረጃ 4 - የኮሮና ቫይረስ በሽታ በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ መኖር አይችልም

እውነታ - የኮሮና ቫይረስ በሞቃት እና እርጥበት አዘል አየር ያሉባቸውን አካባቢዎች ጨምሮ በሁሉም አካባቢዎች ሊተላለፍ ይችላል

መረጃ 5 - በሞቀ ውሀ ሰውነትን መታጠብ በበሽታው እንዳይያዝ ይከላከላል

እውነታ - የሞቀ ውሀ ሰውነትን መታጠብ ኮቪድ-19 በሽታ ከመያዝ አያግድዎትም፡፡ የሚታጠቡበት የገላ መታጠቢያ ውሃ ሙቀት ቀዝቃዛም ሆነ ሙቅ መደበኛ የሰውነትዎ ሙቀት ከ 36.5 እስከ 37 ድግሪ ሴንቲግሬድ ድረስ ይቆያል፡፡

መረጃ 6 - አዲሱ የኮሮና ቫይረስ በትንኞች ንክሻ ይተላለፋል

እውነታ - የኮሮና ቫይረስ በሽታ በወባትንኝ ሆነ በለሌላ አይነት ነፍሳት ንክሻ አይተላለፍም

መረጃ 7 - ነጭ ሽንኩርት መብላት የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመከላከል ይረዳል

እውነታ - ምንም እንኳ ነጭ ሽንኩርትን መመገብ ለጤንነት ጥሩ ቢሆንም እንኳ ከኮቪድ-19 ሊከላከል እንደሚችል የሚያሳይ ምንም መረጃ የለም፡፡

መረጃ 8 - የኮሮና ቫይረስ በሽታ ወጣቶችን ሳይሆን በዕድሜ የገፉ ሰዎችን ብቻ ይይዛል

እውነታ - በሁሉም ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች በኮቪድ-19 ሊያዙ ይችላሉ፡፡

መረጃ 9 - አልኮል መጠጣት ከኮሮና ቫይረስ በሽታ ይከላከላል

እውነታ -  አልኮል መጠጣት በሰውነት ውስጥ ያለን የኮሮና ቫይረስ አያጠፋም፣ ከበሽታም አይከላከልም፡፡

መረጃ 10- አንቲባዮቲኮችን ወይም ፀረ-ባክቴሪያ መድሀኒቶች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እና ለማከም ውጤታማ ናቸው

እውነታ - አንቲባዮቲኮች ወይም የባክቴሪያ መድሀኒቶች በቫይረሶች ላይ አይሰሩም፡፡

የተሳሳተ ዜና / መረጃ ሪፖርት ያድርጉ

የተሳሳተ መረጃ በአቅራቢያዎ ሲኖር ያሳውቁን

መረጃ

  • +251112133499
  • ephieoc@gmail.com
  • 8335

አድራሻ

ፓስተር ፣

አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ

 

[contact-form-7 id="981" title="ሪፖርት"]

አግኙን

  • የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
  • ስዋዚላንድ መንገድ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
  • ስልክ: 0118276796
  • ኢሜል: ephieoc@gmail.com
  • ፖስታ፡ 1242

© 2012, የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ሙሉ መብት የተጠበቀ