የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ ሳይገባ ነበር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን የጀመረው።
በመጋቢት 4 የመጀሪያው የኮቪድ-19 ታማሚ በኢትዮጵያ ከተገኘበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ድረስ 1,936,330 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎል።
የመጀመሪያ ስሞን የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ናሙና ምርመራ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመላክ ነበር ውጤቱን የሚረጋገጠው።
በተሰራው ጠንካራ የላብራቶሪ ማስፋፊያ ስራ እዚሁ ሀገራችን ላይ ናሙናዎችን በመውሰድ የላብራቶሪ ምርመራን ማድረግ ተጀምሮዋል ።
ከዚህም በተጨማሪ በተሰራው የማስፋፊያ ስራ ክልሎችም እዛው በየአካባቢያቸው የላብራቶሪ ምርመራ እንዲያደርጉ ተችሎዋል፡፡
የለይቶ ማቆያም በአዲስ አበባ ብቻ የነበረ ቢሆንም አሁን ክልሎችም የራሳቸውን የለይቶ ማቆያ እንዲያቋቁሙ ተደርጓል በአዲስ አበባ 4 ለይቶ ማቆያ በስራ ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም አሁን ላይ የግል ሆስፒታሎችም የለይቶ ማቆያ አቋቁመው በመስራት ላይ ይገኛሉ ።
ህብረተሰብ ስለ የኮቪድ-19 ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ ፅሑፎችን እና መልዕክቶችን በማሕበራዊ ሚዲያዎች በብዙሀን መገናኛዎች በአደባባይ ላይ በሚሰቀሉ ማስታወቂያዎች ሕብረተሰቡን የማንቃት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል በመስራት ላይም ይገኛል፡፡ ቀድመን በሰራነው የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የመከላከል ስራ ማሕበረሰብን በማንቃት ሊደርስ የሚችለውን ከፍተኛ አደጋ መቀነስ ችለናል::
አሁንም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እራሱን ቀይሮ በአዲስ መልኩ እና የመሰራጨት አቅሙን አጠናክሮ በአለማችን ላይ የብዙሃኑን ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል ይህንንም በመገንዘብ በሀገራችን የከፋ አደጋ እንዳይደርስ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራ እየሰራ ይገኛል::
በመሆኑም “እንድናገለግሎ ማስኮውን ያድርጉ” የሚለውን ንቅናቄ ተቀላቅለው እንዲተገብሩ ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል ።