Categories
Amharic

የቤት ውስጥ ራስን ለይቶ ህክምና (ውሸባ) እና እንክብካቤ (Home Based Isolation and Care) በኢትዮጵያ አገልግሎት መሰጠት ተጀመረ

የቤት ውስጥ ውሸባ እና እንክብካቤ ማለት አንድ የኮቪድ-19 ታማሚ መሆኑ በላብራቶሪ ምርመራ የተረጋገጠ ሰው የህመም ምልክት ሳያሳይ ወይም ቀለል ያሉ የህመም ምልክቶች ያሉት እንዲሁም በቤት ውስጥ መሞላት ያለበትን መስፈርቶች የሚያሞሉ የህብረተሰብ ክፍል የቤት ውስጥ እንክብካቤ ማድረግ ሲጀምር በቤት ውስጥ ውሸባ እንክብካቤ ማድረግ ጀምራል ማለት ነው፡፡
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ በተደረጉ 567,442 የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ምርመራዎች 27,242 በቫይረሱ የተያዙ ታማሚዎች ሲገኙ ከዚህም ውስጥ እስከ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም ከነበሩት 5,000 ታማሚዎች 76 በመቶ ምንም ምልክት የሌለባቸው እና 21 በመቶ መለስተኛ ህመም ያላቸው እና ቀሪውቹ ከባድ እና በፅኑ ህመም ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡
በብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ-19 ምላሽ ማስተባበሪያ የቤት ውስጥ ውሸባ እና እንክብካቤ ክፍል ሀላፊ ዶ/ር ታይካ አለሙ በአሁኑ ሠአት 2000 በላይ የቤት ውስጥ የውሸባ እና እንክብካቤ የሚደረግላቸው ታካሚዎች እንደሚገኙ እና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ከ400 በላይ የሚሆኑት አገግመው መውጣታቸውን ገልፅዋል፡፡ በተጨማሪም በቤት ውስጥ ውሸባ እና እንክብካቤ ጊዜ ከታካሚው ጋር በሚኖረን ግንኙነት ንክኪን ማስወገድ፣ እጃችንን ከአልኮል በተሰራ የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ማፅዳት፣ ከታካሚው ጋር በሚገናኙበት ጊዜ የህክምና የአፍና የአፍንጫ ጭንብል በአግባቡ ማድረግ እደሚኖርብን አሳስበዋል፡፡ እንዲሁም ታካሚዎቹ ማንኛውም የህመም መባባስ ሲኖራቸው ወደ 8335/952 ወይም ለሚከታተላቸው ክፍል በመደወል ማሳወቅ ወይም አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ማግኝት እደሚችሉ አሳውቀዋል፡፡
በቅድሚያ የቤት ውስጥ ውሸባ እና እንክብካቤ ለማግኘት ስለታካሚው ተገቢውን መረጃ መስጠት የሚችል የቤት ውስጥ ተንከባካቢ ወይም የማህበረሰብ በጎ ፍቃደኛ መኖር፣ ቫየረሱ እንዳይሰራጭ ቤቱ በተገቢው ሁኔታ የተዋቀረ መሆን፣ ለታካሚው ቤተሰብ በቂ የአፍና አፍንጫ ጭንብል፣ ጓንት መኖሩን ማረጋረጥ የምግብ እና መሰረታዊ አቅርቦቶች ሞሟላት በተጨማሪም ተንከባካቢው እንዲሁም ታማሚው ተጓዳኝ በሽታ እንደሌለበት ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ ህብረተሰቡ የቤት ውስጥ ውሸባ እና እንክብካቤ መጀመሩን አውቆ ከጤና ባለሞያዎች የሚሰጠውን ምክር በሚገባ መተግበር እንዳለበት እና ለቫይረሱ ስርጭት ምክንያት ባለመሆን እንዲጠነቀቁ ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *