የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ያገኛል፡፡ከዚህም ውስጥ የላብራቶሪ ማስፋፊያ ስራ አንዱ ነው፡፡በተሰራው የላብራቶሪ ማስፋፊያ ስራ ከአንድ ላብራቶሪ ምርመራ ተቋም በመነሳት በምርምር ተቋማት፤በክልል ላብራቶሪዎች ፤ በዩኒቪርቲዎች እንዲሁም ከግል ተቋማት ጋር በመተባበር የ ኮቪድ-19 ምርመራ ተቋማትን ማስፋፋቱ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሰረት የግል ተቋማት አስፈላጊውን መስፈርት ካሟሉ በኃላ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ፍቃድ ይሰጣቸዋል። ይህንን ፍቃድ ካገኙ 15 የግል ተቋማት 13 ነባር የግል ተቋማት ሲሆኑ 2 አዲስ መስፈርቱን አሟልተው የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እና የውጤት የሰርተፊኬት የሚሰጡ የግል ተቋማት በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡
ይሁን እንጂ በቅርቡ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እናደርጋለን እስከ 6 ሰዓትም ውጤት እናሳውቃለን እያሉ ማስታወቂያ የሚያሰራጩ ተቋማት መኖራቸውን ደርሰንበታል፡፡
ስለሆነም ተገቢውን መስፈርት ሳያሟሉ ምርመራ እናደርጋለን የሚሉ ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማህበረሰቡም መስፈርቱን አሟልተው እውቅና በተሰጣቸው ተቋማት ብቻ አገልግሎት እንዲያገኙ እያሳሰበ አዲስ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋማት ሲኖሩ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ መስፈርቱን አሟልተው የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ የሚሰጡ የግል ተቋማት ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ናቸው።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ
#COVID19Ethiopia
#NOMASKNOSERIVCE