በኢትዮጵያ እስከ ትላንትናው እለት ድረስ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 176,618 ግለሰቦች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ 2,555 ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።በዛሬው እለት በደረሰን መረጃ ብቻ 8 ያህል ግለሰቦች ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
እስከ ትላንትናው ዕለት 531 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ ተይዘው በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ይህ ቁጥር ኮቪድ-19 ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ ጀምሮ የመጀመሪያው ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።ከእነዚህም ውስጥ 66 ግለሰቦች በአርቴፊሻል ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡እስከ ትላንትናው እለት ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የገቡ፤በፅኑ ህክምና ማዕከል ድጋፍ ሲደረግላቸው ከነበሩት ግለሰቦችውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገቡት ክልሎችን ስንመለከት ፦
*በአዲስ አበባ 409
* በኦሮሚያ ክልል 57
*በስዳማ ክልል 33 ግለሰቦች ወደ ፅኑ ህሙማን መርጃ ክፍል የገቡ እና በፅኑ ህክምና ማዕከል ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው፡፡
በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ታማሚዎች በባለፈው ወር በአማካኝ 260 ነበር፤ አሁን ካለው ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ጨምሮዋል፡፡ በአሁን ጊዜ የህክምና ማዕከላት ከፍተኛ የሆነ የአልጋ፤አርቴፊሻል ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ እና ኦክስጂን እጥረት እያጋጠማቸው ይገኛል፡፡
የኮቪድ-19 ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተያዙ ፅኑ ህሙማን አርቴፊሻል ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው፡፡
ስለሆነም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኝ ግለሰብ ፤ ቤተሰብ ፤ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፤ የሐይማኖት ተቋማት ፣ ሲቪክ ማህበራት ፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፤ የጤና ባለሙያዎች ፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ማስክ ማድረግ ፣ የእጃቸውን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ተገቢውን የጥንቃቄ መንገዶችን በመተግበር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንድንከላከል የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥሪውን ያቀርባል።
#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ
#COVID19Ethiopia
#COVID19VACCINE
#NOMASKNOSERIVCE