የኮቪድ-19 በሽታ በማንኛውም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን በብዙ ህመም ውስጥ እንዲገኙ አልፎም ለብዙዎች ህይወት ህልፈት ምክንያት ሆኗል፡፡ ለትውልድ ታሪክ፣ ቅርስ እና ባህልን የሚያስተላልፉልን በተለይም እድሜያቸው ከ55 በላይ የሆኑ አባቶቻችን እና እናቶቻችን በበሽታው ምክንያት ህይወታቸውን በየቀኑ ከሚያልፉት መካከል ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ የትላንት ታሪካችንን የሚያስተምሩልን፣ ለዛሬ ማንነታችን መሰረት የሆነውን ባህላችን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያሻግሩትን ታላላቆቻችን ጀግኖችን በምንዘክርበት በዚህ ወቅት ጤናቸውንም እንጠብቅ ዘንድ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡
ባሳለፍናቸው ሁለት ወራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሌሎች ሀገራት መቀነስን ቢያሳይም ይህ ግን በእኛ ሀገር የተቃራኒውን መንገድ ይዞ በመገስገስ ላይ ይገኛል፡፡ እንደማሳያነት በአህጉራችን ግንባር ቀደም የኮቪድ-19 ቁጥር ሪፖርት የምታደርገው ደቡብ አፍሪካ በተከተሉት ጥብቅ የመከላከያ መንገዶች በጥር ወር ውስጥ በቀን እስከ 21,000 በቫይረሱ የተያዙ እና 755 ግለሰቦች ሞት በመቀነስ በየካቲት ወር 1,168 በቫይረሱ የተያዙግለሰቦች እና 157 ግለሰቦች ሞት ሪፖርት ማድረግ ችለዋል፡፡ ይህም ከሚያዙት የሰው ቁጥር 15 እና ከሚሞቱት ሰዎች 5 እጥፍ ለውጥ ያሳያል፡፡
በሀገራችን ወረርሽኙን ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ያለ ሲሆን እንደምሳኔነት እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ ንቅናቄ እና የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፤ባሳለፍነው ወራት የተስተዋሉት በየጊዜው በመቀነስ ላይ የሚገኝው የኮቪድ-19 መከላከያ መንገድ ትግበራ፣ የሰው መሰባሰብ የሚበዛባቸው በዓላት፣ ሰርግን ጨምሮ ያሉ የማህበራዊ የኑሮ ዝይቤዎች፣ የመንገድ ላይ ሰልፎች እንዲሁም ሌሎችም የኮቪድ-19 ስርጭትን እንዲጨምር ምክንያት ከሆኑት ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ባሳለፍነው የፈረንጆች የጥር ወር ውስጥ ከተደረጉ 144,587 ምርመራዎች 12,028 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 145 የህይወት ህልፈቶችም በዚህ ወር ተመዝግቧል፡፡ በየካቲት ወር ከተደረጉ 172,035 ምርመራዎች ውስጥ 21,422 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ እና 272 ህልፈቶች ሪፖርት ተደርጓል፡፡ እነዚህንም ወራት በምናወዳድርበት ወቅት የተያዙ ሰዎች ቁጥር 78 በመቶ እንዲሁም በሞት ቁጥር 88 በመቶ መጨመር አሳይቷል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ፤ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እንዲሁም በኮቪድ -19 ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ እያንዳንዱ ግለሰብ፤ ቤተሰብ፤ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ የሐይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ የጤና ባለሙያዎች፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ማስክ ማድረግ ፣ የእጃቸውን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ተገቢውን ጥንቃቄ እዲያደርጉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያሳስባል፡፡
#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ
#COVID19Ethiopia
#NOMASKNOSERIVCE