Categories
Amharic

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር ከሁለት መቶ ሺህ አለፈ

የኮቪድ-19 ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱ ከታወቀ አንድ አመት አልፎታል። በእነዚህ ጊዜያት ለ2.3 ሚሊዮን በላይ ግለሰቦች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከ200,000 በላይ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።እስካሁን 154,323 ከኮቪድ-19 ቫይረስ አገግመዋል።

በትላንትናው ዕለት 7,250 ግለሰቦች የኮቪድ-19 ምርመራ ያደረጉ ሲሆን 1,769 ግለሰቦች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ይህም ማለት ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 24 ወይም (24%) ግለሰቦች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። 805 ግለሰቦች ደግሞ በፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ እየታከሙ ይገኛሉ። ለ 2,801 ግለሰቦች ሕይወት ሕልፈት እና ለብዙዎች ደግሞ ማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ስነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ቀውሶችን አስከትሏል። ከዚህም የከፋ ችግር እንዳይገጥመን ማስክዎትን በአግባቡ በማድረግ የእጅዎን ንፅህና እንዲሁም እርቀትዎን በመጠበቅ ወገኖውን ይታደጉ ፤ አሁንም ልባችንን እንጂ እጃችንን ለሰላምታ አንዘርጋ፡፡

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia

#COVID19VACCINE

#NOMASKNOSERIVCE  

https://t.me/EthPHI

https://www.facebook.com/EPHIEthiopia https://twitter.com/EPHIEthiopia?s=09

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *