በአለም ዙሪያ በየደቂቃው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያዙ እና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ በኢትዮጵያ እስካሁን 3,148,930 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 293,737 ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ፤ በትላንትናው ዕለት 21 ግለሰቦች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን እስካሁን 4,539 ግለሰቦች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በትላንትናው ዕለት ነሀሴ 14/2013 ከተመረመሩት 6‚814 ውስጥ 1‚006 ግለሰቦች ቫይረሱ ሲኖርባቸው ፤ ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች 15 ግለሰቦች ወይም (15%) መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህ በኮቪድ-19 የመያዝ ምጣኔ ከ107 ቀናት በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ቫይረስ የሚያዙ ፤ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ እንዲሁም በኮቪድ -19 ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ እያንዳንዱ ግለሰብ ፤ ቤተሰብ ፤ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፤ የሐይማኖት ተቋማት ፤ ሲቪክ ማህበራት ፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፤ የጤና ባለሙያዎች ፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ማስክ ማድረግ ፤ የእጃቸውን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ተገቢውን ጥንቃቄ እዲያደርጉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያሳስባል፡፡
#COVID19Ethiopia
#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ
#NOMASKNOSERIVCE