Categories
Amharic

በትላንትናው ዕለት በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር ከ84 ቀናት በኋላ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ-19 ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህም በበሽታው የሚያዙ ፣ በጽኑ የሚታመሙና ህይወታቸውን የሚያጡ ወገኖቻችን ቁጥር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ በከፍተኛ መጠን ጨምሯል።

በትላንትናው ዕለት ለ7‚598 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 687 ግለሰቦች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ማለት ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 9ኙ (9%) የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። 270 ግለሰቦች ደግሞ በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ 

በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በዚህ ፍጥነት እጨመረ የሚሄድ ከሆነ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ይጨምራል። ይህ ደግሞ በኮቪድ-19 ህክምና ማዕከላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የአልጋ ፣ ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ እና ኦክስጂን እጥረት ሊያስከትል ይችላል፡፡

በኮቪድ-19 ቫይረስ የሚያዙ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ እና ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦች ቁጥር እያሻቀበ ይገኛል።ስለሆነም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ግለሰቦች፤ ቤተሰቦች፤ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፤ የሐይማኖት ተቋማት ፣ ሲቪክ ማህበራት ፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፤ የጤና ባለሙያዎች ፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ማስክ በማድረግ ፣ የእጃቸውን ንጽህና በተደጋጋሚ በመጠበቅ ፣ በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የከፋ ችግር እንዳያስከትል በጋራ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥሪውን ያቀርባል።

#COVID19Ethiopia #እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *