Categories
Amharic

ማብራሪያ

መጋቢት 16  ቀን 2013 ዓ.ም በማህበራዊ ድረ-ገጽ ያወጣነው የኮቪድ-19ን እለታዊ  ሁኔታ የሚገልጸው ዜና በተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች በተለያየ መንገድ መዘገባቸውን እና በማህበረሰቡ ዘንድ ብዥታ መፈጠሩን ተገንዝበናል፡፡ ስለሆነም በዜናው ላይ  ማብራሪያ መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ የሚከተለውን አጭር ማብራሪያ ለመስጠት እንወዳለን፡፡

 መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም ምርመራ የተደረገላቸው  ሰዎች በተለያዩ  ምክንያቶች ወደ ጤና ተቋም ሄደው ህክምና ላይ የነበሩ ፣ በማህበረሰብ ቅኝት እና ዳሰሳ አማካኝነት ቫይረሱ ካለባቸው ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው፣ የበሽታው ምልክት ታይቶባቸው  በጤና ተቋማት ናሙና የሰጡ  እና ወደ ውጭ ሀገር ለመሄድ የኮቪድ -19 ናሙና ምርመራ ያደረጉ ናቸው፡፡ በእለቱ የኮቪድ-19 ምርመራ ከተደረገላቸው  7,659 ግለሰቦች ውስጥ በ1,981 ሰዎች ላይ ወይም  ከ100 ግለሰቦች 26  (26%) ያህሉ ኮቪድ-19 ቫይረስ እንዳለባቸው ተረጋግጧል፡፡ይህም  በእለቱ  ምርመራ ካደረጉ ከ አስር ሰዎች ሶስቱ ወይም ከሶስት  ሰዎች  አንዱ በቫይረሱ መያዛቸውን ያሳያል፡፡ ይህ ማለት የበሽታው አጠቃላይ ስርጭት ማህበረሰቡ ውስጥ በዚህ ልክ ነው ማለት እንዳልሆነ እየገለጽን ይህንን እለታዊ መረጃ ለህብረተሰቡ መግለጽ ያስፈለገው ግለሰቦች፣ ህብረተሰቡ፣ የተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ማህበራት እና ድርጅቶች መረጃውን በመጠቀም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት መጨመሩን በመረዳት ተገቢውን የበሽታውን መከላከያ መንገድ በመተግበር እና ሌሎችም እንዲተገብሩ ለማስቻል ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ እና የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ለማሳሰብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ #እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *