ኮቪድ-19 ከሰው ወደ ሰው እንዴት ይተላለፋል?

ኮቪድ-19 ከአፍ በሚረጩ እርጥበት አዘል ብናኞች በኩል በከፍተኛ ሁኔታ ይተላለፋል።

መተላለፊያ

ቫይረሱ የበሽታውን ምልክት ከሚያሳዩ ሕመምተኞች ጋር በሚኖር ንክኪ በከፍተኛ ሁኔታ ይሰራጫል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ግን ቫይረሱ በውስጣቸው ያለ ነገር ግን የበሽታውን ምልክት ማሳየት ያልጀመሩ ሰዎች በሽታውን እንደሚያስተላልፉ አንዳንድ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለሆነም በዓለም ጤና ድርጅት መመሪያ መሰረት፤ በአገራችን ውስጥ ከበሽተኛው ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ማፈላለግ የሚደረገው ታካሚዎች የበሽታውን ምልክት ከማሳየታቸው  48 ሰዓታት በፊት ካገኟቸው  እና ቀጥተኛ ንክኪ የነበሯቸውን ሰዎች በዚህ የበሽታውን መከላከል ስርአት ውስጥ በማካተት ነው፡፡

ቫይረሱ በመጀመሪያ ሰዎች ከእንስሳት ጋር ባላቸው ግንኙነት ከእንስሳት ወደ ሰው ይተላለፋል የሚል ግምት ነበር፡፡ ይህም ግምት አብዛኛዎቹ የመጀመሪያ ታማሚዎች በቻይና በውሃን ግዛት በሚገኘው የዃናን ገበያ ውስጥ የባህር ምግብ እና እንስሳት ገበያ ላይ የነበሩ ስለሆነ ነው፡፡ ሆኖም የበሽታው ስርጭት ገበያው ከተዘጋ በኋላ በመቀጠሉ ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው መተላለፉ ግልፅ ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን ስለ መተላለፊያ መንገዶች ጥናቶች እየተደረጉ ቢሆንም እስካሁን ባለው መረጃ  SARS CoV-2 የሚተላለፈው በበሽታው የተያዘ ሰው በሚያስነጥስ፣ በሚያስልበት ጊዜ ወይም በንግግር ጊዜ በሚመረቱ በአይን  በማይታዩ እርጥበት ያለው ብናኝ ነው ተብሎ ይታመናል። እነዚህ በአይን  በማይታዩ እርጥበት ያለው ብናኞች በመጠናቸው የተነሳ ከ 2 ሜትር ርቀት ባሻገር በአየር ውስጥ አይቆዩም።

ቀጥተኛ ንክኪ

በተጨማሪም ጥናቶች ቫይረሱ በተለያዩ እቃዎች ላይ ሊገኝ እንደሚችል እና ከበሽተኞቹ ጋር ከሚኖር ቀጥተኛ ንክኪ ብቻ ሳይሆን በአከባቢው በተበከሉት ቁሳቁሶች አማካይነት ሊተላለፍ እንደሚችል ያመለክታሉ፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት ሆስፒታሎች ጋር የተዛመደ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሲሆን የጤና  ባለሞያዎች ለታማሚዎች ከሚያደርጓቸው የህክምና ሂደቶች አኳያ ቫይረሱ በአየር ሊሰራጭ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ፡፡

በእርጥበት አዘል ብናኝ

በተጨማሪም ጥናቶች ቫይረሱ በተለያዩ እቃዎች ላይ ሊገኝ እንደሚችል እና ከበሽተኞቹ ጋር ከሚኖር ቀጠተኛ ንክኪ ብቻ ሳይሆን በአከባቢው በተበከሉት ቁሳቁሶች አማካይነት ሊተላለፍ እንደሚችል ያመለክታሉ፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት ሆስፒታሎች ጋር የተዛመደ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሲሆን የጤና  ባለሞያዎች ለታማሚዎች ከሚያደርጓቸው የህክምና ሂደቶች አኳያ ቫይረሱ በአየር ሊሰራጭ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ፡፡

ከእናት ወደ ልጅ መተላለፊያ

በእርግዝና ወቅት የኮቪድ-19 በሽታ ከእናት ወደ ልጅ ስርጭትን በእርግጠኛነት ለመወሰን ተጨማሪ ጥናቶች ቢያስፈልጉም እስካሁን ድረስ ሳይንቲስቶች ነፍሰ ጡር ሴቶች ለኮቪድ-19 የበለጠ ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያምናሉ፡፡ ይህም ማንኛውም ነፍሰጡር እናት ለመተንፈሻ አካላት በሽታ ተጋላጭ መሆናቸው አንዱ ምክንያት ነወ፡፡ እስካሁን በቫይረሱ በተያዙ ነፍሰጡር እናቶች ላይ በተደረጉ ጥናቶች ምንም እንኳን ያለግዜያቸው ምጥ እንደ ጀመራቸው ቢስተዋልም በሽታው ከእናት ወደ ልጅ ቀጥታ እንደሚሰራጭ የሚያሳይ ምንም አይነት መረጃ አልተገኘም፡፡

ሌሎች መተላለፊያዎች

በተጨማሪም ከሰገራ፣ የሆድ እቃ፣ ምራቅ፣ ሽንት እና ከታካሚ ዓይኖች ከሚወጡ ፈሳሾች  ውስጥ ቫይረሱን መለየት እና ማግኘት ተችሏል፡፡ ምንም እንኳ ቫይረሱ ከነዚህ የሰውነት ፈሳሾች ላይ ቢገኝም፤ በሽታው ከሳንባ ከሚወጣ ጠብታ ከሚኖረን ንክኪ በኋላ ባልታጠበ እጅ ከአይን፣ ከአፍንጫ እና ከአፍ በምናደርገው ንክኪ ከመተላለፉ ውጪ፤ እንደዚህ ካሉ የሰውነት ፈሳሾች ጋር በሚኖር ቀጥታ ንክኪ በሽታው መተላለፍ  አለመተላለፉን የሚያሳይ መረጃ የለም፡፡

ምርመራ

ሳይዘገይ የሚደረግ ምርመራ በተለይም ደግሞ ከባድ የመተንፈሻ ችግር ለሚታይባቸው ሰዎች ትልቅ መፍትሔ አለው፡፡የኮቪድ-19 በሽታ ለመለየት የሞለኪዩላር ምርመራ የሚደረግ ሲሆን ለዚህም ወሳኝ የሆነው ለምርመራው የሚወሰደው የናሙና አይነት እና ናሙናውን የምንወስድበት ጊዜ ነው፡፡ ምንም እንኳ ከበሽታው ጋር ያሉ ተጓዳኝ በሽታዎችን ለመለየት ሌሎች ምርመራዎች ቢያስፈልጉም ለኮቪድ-19 ሞለኪዩላር ምርመራ ትክክለኛ አይነት ናሙና ከትክክለኛ ቦታ እና በትክክለኛ ጊዜ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ የሞለኪዩላር ምርመራ ዓለማችን ከደረሰችባቸው ውጤታማ እና ተመራጭ ምርመራ አንዱ ነው፡፡ ቫይረሱን ከመተንፈሻ አካል ማለትም ከአፍንጫ፣  ከጉሮሮ፤ ለመተንፈሻ አካል እርዳታ ወደ ሳንባ ከሚገባ ቱቦ የሚወሰድ ናሙና ወይም ኢንዶትራኪያል አስፓይሬት (endotracheal aspirate) ብሮንኮ አልቪዮላር ላቫጅ (broncho alveolar lavage) እንዲሁም ከደም ሊወሰድ ይችላል፡፡ በሽታውን ለማግኘት እየተከናወነ ያለው ሌላ የምርመራ ዘዴ ደግሞ የሲቲ ስካን ምርመራ ሲሆን ታማሚው ከሚያሳየው የበሽታ ምልክቶች እና የላቦራቶሪ ግኝቶች ጋር በማጣመር በሽታው ላይ መድረስ ያስችላል። ይህ የሲቲ ስካን ምርመራ የበሽታውን ምልክት በማያሳዩ አንዳንድ ታማሚዎች ላይ በሽታውን ለማግኘት እንደሚያስችል አንዳንድ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

አግኙን

  • የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
  • ስዋዚላንድ መንገድ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
  • ስልክ: 0118276796
  • ኢሜል: ephieoc@gmail.com
  • ፖስታ፡ 1242

© 2012, የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ሙሉ መብት የተጠበቀ